ለህብረት መረዳጃ ማህበር የቦርድና የመማክርት ምክርቤት እጩ አባላት     ቀን January 11, 2023

 
የሕብረት መረዳጃ ማህበር ጊዜያዊ አስተዳደር የከበረ ሰላምታውን ያቀርባል። በዲሴምበር 24, 2022 በተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ለቦርድና ለመማክርት ምክርቤት የሚያገለግሉ አባላትን መልምሎ እንዲመድብ ሰልጣን መስጠቱ ይታወሳል። እርሶም ለማኅበሩ የቦርድ እና የመማክርት ምክር ቤት አባል ሆነው ለማገልገል ፈቃደኛ ስለሆኑ ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
 
ከእጩ ግለሰቦች ተጨማሪ መረጃዎችን ማሰባሰብ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ተያይዞ የሚገኘውን ፎርም በጥንቃቄ በመሙላት የተጠየቁ መረጃዎች እንዲሰጡን እየጠየቅን ጊዜያዊ አስተዳደሩ መረጃዎችን በማጠናቀር ለማህበራችን አዲስ የቦርድ እና የመማክርት ምክር ቤት በመመስረት ማህበሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲዋቀር ይደረጋል። ለዚህም የእርሶ ሙሉ ተሳትፎና ትብብር ስለሚያስፈልግ የበኩልዎን ድጋፍ እንጠይቃለን።
 
በመሆኑም የተዘጋጀውን ቅጽ በኦንላይን እንዲሞሉ ከዚህ በታች ያለውን የማገናኛ ሊንክ ይጫኑ።
 
በተጠየቁት ርዕሶች ላይ የሚቻልዎትን መረጃ እንዲሰጡን እየጠየቅን አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ተጨማሪ መረጃ ለመላክ ከቅጹ መጨረሻ ላይ መረጃዎን እንዲያይዙና እንዲልኩልን እንጠይቃለን። ቅጹን በእንግሊዝኛ ወይንም በአማርኛ መሙላት ይችላሉ። 
ይህን ፎርም በደረሶት የኦን ላይን ሊንክ ከ January 21,2023 በፊት እንዲሞሉና እዲያሰገቡ በትህትና እንጠይቃለን፡፡ 
 
ጥያቄ ካለዎት ከታች በተመለከተው ኢሜል በመላክ ወይም ስልክ በመደወል ተጨማሪ ማስረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ማሳሰቢያ፡ ክፍት የሃላፊነት ቦታዎችን የሰራ ዝርዝር ለማግኘት በማህበራችን ድረገጽ ውስጥ የመተዳደሪያ ደንቡንና የማህበሩን የውስጥ አሰራር የሚገልጸውን ሰነድ ለማግኘት ከታች ያለውን አገናኝ ሊንክ ይጫኑ።
 
ከአክብሮት ሰላምታ ጋር የኅበረት መረዳጃ ማህበር ጊዜያዊ አስተዳደር
Hebret Mutual Aid Society, Inc–7961 Eastern Ave NW Ste# 301, Silver Spring, MD 20910 
Email: 

Hebret2021@gmail.com

 ስልክ፡ (240) 641-4917