ለኅብረት መረዳጃ ማህበር አባላት በሙሉ
2025 የህብረት መረዳጃ ማህበር የአዲስ አባላት ምዝገባ ስርዓት
የዚህ መመሪያ ዋና ዓላማ ማህበሩ የተቋቋመበት ህግ እንዳለ ሆኖ አዲስ የሚመዘገቡ አባላት
በምዝገባ ወቅት ሊያሟሉዋቸው የሚገቡ መስፈርቶችን እና የምዝገባ ስርዓትን በከፊል ለማሳወቅ
እንዲሁም አፈፃፀሙም በዚሁ መሰረት የሚከናወን መሆኑን ለማሳየት ነው።
1. ምዝገባ የሚካሄደው ቀድሞ በደረሰ ቅደም ተከተል ይሆናል።
2. ማህበሩ የፖለቲካ፣የሀይማኖት፣የዘር፣የፆታ፡ወገንተኝነት የሌለው እና የእድሜና ሌሎች ልዩነቶችን
የማያደረግ በሜሪላንድ ህግ ለትርፍ ያልተቋቋመ ማህበር መሆኑን መገንዘብ።
3. የህ.መ.ማ ዓባል ለመሆን ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ እድሜው ከ 18
ዓመት በላይ የሆነ በራሱ አቅም ህጋዊ ውሳኔዎችን ማድረግ የሚችል ከ18 ዓመት በታች ከሆነ
በወላጆች ውክልና እና ሃላፊነት ድምፅ የማይሰጥ ዓባል ሆኖ መመዝገብ የሚችል ሲሆን ማንኛውም
ዓባል በዋሽንግተን ዲሲ፣በሜሪላንድ እና ቨርጂኒያ አካባቢ የሚኖር ሆኖ የሚከተሉትን ማሟላት
ይኖርበታል።
3.1 በማህበሩ በተዘጋጀው የማመልከቻ ፎርም ላይ ያሉትን መረጃዎችን በጥንቃቄ
አሟልቶ ማመልከቻውን በአካል ማቅረብ ፣
3.2 ከላይ በተገለፁት አካባቢ የሚኖሩ ለመሆኑ ከመንግሥት የተሰጠ መታወቂያ ይዞ
በአካል ቀርቦ መመዝገብ፤
3.3 በመታወቂያው ላይ በተገለፀው አድራሻ ለመኖሩ ማረጋገጪያ የቤት ኪራይ
ውል፣የቤት ባለቤትነት ሰነድ፤ወቅታዊ የጋዝ ፣ የውሀ፣የኤሌክትሪክ ደረሰኝ ወይም
ማንኛውም ከመንግስት የተሰጠ ሌላ መረጃ ማቅረብ፤
3.4 በማህበሩ በተዘጋጀው የተወካይ መጠሪያ ቅፅ ላይ በተገለፀው መሰረት
ሁሉንም በትክክል ሞልቶ በፓብሊክ ኖትሪ አስደርጎ ማቅረብ፤ ወይም በመዝጋቢው
እና በወቅቱ በተገኙት የቦርድ አባል ፊት ቀረቦ ቅፁ ላይ መፈረም ፤ሁሉም ተወካዮች
በአሜሪካ የሚኖሩ መሆን አለባቸው።
3.5 አዲስ አመልካች የአንድ ጊዜ የመመዝገቢያ ፣ የማይመለስ የመመዝገቢያውን
10% የአስተዳደር ወጪ እና አመታዊ የአባልነት ክፍያዎች እንደሚከፍል ማወቅ
ይኖርበታል።
4. ማንኛውም አዲስ አመልካች የአባልነት ማመልከቻው ተቀባይነት ካገኘ የአባልነት መብት እና
ግዴታን በተመለከተ በማህበሩ መተዳደሪያ ህግ እና የአሰራር መመሪያዎች መሰረት የሚፈፀም መሆኑን
ሲፈርም በምዝገባ ወቅት ማረጋገጡን ግንዛቤ እንዲወሰድ ።
5. ማንኛውም አዲስ አባል የአባልነት ማመልከቻው ተቀባይነት ካገኘ የአንድ ጊዜ መመዝገቢያ ክፍያ
እንዲሁም በየዓመቱ ዓመታዊ የአባልነት ክፍያ ለመክፈል መስማማቱን እንዳረጋገጠ ግንዛቤ
እንዲወስድ።
6. ማንኛውም የአባልነት ማመልከቻው ተቀባይነት ያገኘና ተገቢውን ክፍያ ያጠናቀቀ አዲስ አባል
የማህበሩ ተጠቃሚ መሆን የሚችለው ከ180(ከአንድ መቶ ሰማንያ) ቀናት የቆይታ ጊዜ በኋላ
መሆኑን መረዳቱ እና ማርጋገጡ ግንዛቤ እዲውሰድ ።
7. አመልካቾች ማመልከቻቸው ተቀባይነት ካላገኘ ውሳኔው በማመልከቻው ላይ በሰጡት ኢሜይል
፣ስልክ ቁጥር ወይም አድራሻ የሚገለፅ ሲሆን በተጨማሪም መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ የአገልግሎት
ድጋፍ ዴስክን 240-641-4917 በመደወል እና በኢሜል hebret2021@gmail.com
መጠየቅ የሚቻል ይሆናል ።
8. ምዝገባውን ለማካሄድ በማህበሩ የተመደበው አካል አመልካቹ በመመሪያው መሰረት
ማመልከቻውን ያሟላ መሆኑን ያረጋግጣል ፤ያልተሟላ ከሆነ አመልካቹ እንዲያሟላ ያደርጋል
፤በዚሁም መሰረት የተዘጋጀውን ቅፅ አመልካቹ ፣ቅፁን ያስሞላው አካል እንዲሁም በወቅቱ የተገኘ
የማህበሩ የቦርድ አባል ይፈርሙበታል ። በማንኛውም ሁኔታ ያልተሟላ ማመልከቻ ተቀባይነት
የለውም።
9. የሚቀርቡ የተወካዮች ወይም የተመዝጋቢ ማስረጃዎች የተዛቡ ወይም የተሳሳቱ እንዳይሆኑ
አመልካቹ አሰፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ እናሳስባለን፡፤
10. ወደፊት በሂደት የመታወቂያ፣ የአድራሻ ወይም በአባልነት ምዝገባ ወቅት ለማህበሩ የተሰጡ
መረጃዎች ለውጥ ቢደረግባቸው አባሉ በመተዳደሪያ ደንቡ በተገለፀው 30(ሰላሳ ቀናት) ውስጥ
መረጃዎቹን ይዞ በመቅረብ ወቅታዊ ማድረግ እንዳለበት እናሳስባለን።
11. ማንኛውም ተቀባይነት ያገኘ አዲስ አባል የማህበሩን የመተዳደሪያ ህግ እና መመሪያዎች አንብቦ
መብት እና ግዴታዎችን እንዲያውቁ እያሳሰብን ማንኛውንም መረጃ ከማህበሩ ድረገፅ ላይ የሚያገኝ ሲሆን
ለማንበብ ለማተም እና ሌሎች መረጃዎች ለማግኘት የራስዎን ፖርታል በድረገፁ ላይ እንዲኖርዎት
እናበረታታለን ።
የኅብረት መረዳጃ ማህበር አስተዳደር ቦርድ
