የመተዳደርያ ደንብ ለማሻሻል የወጣ ማስታወቂያ

ለኅብረት መረዳጃ ማህበር እጩ አባላት በሙሉ

በማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ በፀደቀዉ የህብረት መረዳጃ ማህበር መተዳደሪያ ደንብ አንቀፅ 4 ተ.ቁ 4.1.6 እንደተደነገገው፡
Full Membership. One Hundred and Eighty (180) days after an application has been reviewed and approved and all dues/fees are paid in full, the applicant shall be considered a member and
will be issued a membership ID. Only those members whose dues are current will be entitled to all privileges and benefits of the Society
“ሙሉ አባል፡ የአባልነት ማመልከቻው ተመርምሮና ተቀባይነት አግኝቶ አስፍላጊውን ክፍያ ካጠናቀቀ ከአንድ መቶ ሰማኒያ (፩፹) ቀናት በኋላ እንደ አባል ተቆጥሮ የአባልነት መታወቂያ ይሰጠዋል። የሚጠበቅባቸዉን ክፍያዎች በወቅቱ የሚያጠናቅቁ አባላት ብቻ ማህበሩ የሚስጠውን ጥቅም የማግኘት መብት ይኖራቸዋል” ይላል።

ነገር ግን የቀድሞው የሁሉም ለአንድ ማህበር አባል የነበሩና ቀደም ብለው የህብረት መረዳጃ ማህበር የአባልነት መስፈርቶችን አሟልተው የማህበሩ ቦርድ በጠየቀው መሰረት የአባልነት ክፍያቸዉን ያጠናቀቁና የአባልነት መታወቂያ የሚሰጣችው አመልካቾች ይህ ድንጋጌ ሳይመለከታቸው የማህበሩ ሙሉ አባልና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የጠቅላላ ጉባዔውን
የተለየ ውሳኔ አስፈልጓል።

በዚህም መሰረት የኅብረት መረዳጃ ማህበር ቦርድ ይህን የውሳኔ ሃሳብ ለጠቅላላ ጉባዔው ያቀርባል። ይህን ተግባራዊ ለማድረግ ወደ ማህበሩ ፖርታል መግቢያ ሊንክ በኢሜልና በቴክስት ይላካል፡፡ እጩ አባላት መተዳደሪያ ደንቡንና የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ እንዲያነቡ እናሳስባለን። በመቀጠልም እጩ አባላት ከቅዳሜ ማይ (May) 6 ቀን 2023 ዓም ከጠዋቱ 9 AM እስከ ሰኞ ሜይ (May) 8 ቀን 2023 ዓም 5 PM ድረስ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ለማጽደቅ ድምጽ ይሰጣሉ። ስለሆነም እጩ አባላት በኦን ላይን የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ እንዲያጸድቁ ድምጽ መስጫ አገናኝ (ሊንክ) ከ Securedvoting.com ይደርሳቸዋል። በዚህ ቀን ምርጫችሁን እንድታሳውቁ አጥብቀን እናሳስባለን፡፡
ድምጽ ከሰጡት እጩ አባላት ከ75% በላይ ከተስማሙበት የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ይጸድቃል። እጩ አባላት በተሰጠው የጊዜ ገደብ የድምጽ መስጫው ሊንክ በኢሜልና በስልክ እንደደረሳቸው ወዲያውኑ ድምጽ እንዲሰጡ እናሳስባለን፡፡ የድምጽ መስጫው ምን እንደሚመስልና እንዴት እንደሚሰራ የሚያብራራ መመሪያም አብሮ ይላካል፡፡
ማሳሰቢያ
እጩ አባላት ማህበሩ ስራውን መቼ እንደሚጀምር ለመጠየቅ በተደጋጋሚ መልዕክት ይደርሰናል። ክላይ የቀረበው የውሳኔ ሀሳበ በጠቅላላ ጉባኤው ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ ማህበሩ ሙሉ ስራውን ይጀምራል።

የኅብረት መረዳጃ ማህበር አስተዳደር ቦርድ

Instruction on how to vote.

የምዝገባ ክፍያ ማስታወቂያ

ለኅብረት መረዳጃ ማህበር አመልካቾች በሙሉ March 20፣ 2023ዓ ም
አዲሱ የኅብረት መረዳጃ ማህበር አስተዳደር ቦርድ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ቦርድ ከተሰየመበት ከፌብሯሪ አስራ አራት(February 14) ቀን 2023 ዓም ጀምሮ ከዚህ በታች ያሉትን ተግባራት አከናውኗል።
1) ማህበሩ ሰራውን ለመጀመር እንዲችል ጊዜያዊ አስተዳደሩ አስፈላጊው ዝግጅት አድርጎ የተለያዩ ሰልጠናዎችንና የስራ ልምዶችን ቀስሟል
2) የቦርዱ አመራር አራት 4 ጊዜ ስብሰባዎችን አድርጓል፣ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔዎችን አስተላልፏል
3) ከጊዜያዊ አስተዳደሩ የማህበሩን ጽሕፈት ቤትና ንብረት ፌብሯሪ 25 ቀን 2023 ዓ ም ተረክቧል
4) የባንክ አካውንቱን ተረክቧል
በመቀጠልም ማህበሩን ሥራ ለማስጀመር እንዲቻል ምዝገባ እና የውክልና ቅጽ ልከው ያጠናቀቁ 1,204 እጩ አመልካቾችን ሙሉ አባል ማድረግ እና ሰርትፊኬት መስጠት ይጠበቅበታል። ስለሆነም እያንዳንዱ አመልካች እጩ አባል በአዲሱ ኅብረት መረዳጃ ማህበር መተዳደሪያ ደንብ መስረት ተጠቃሚ እንዲሆን ለሥራ ማስጀመሪያ $140(አንድ መቶ አርባ ዶላር) ፣ ለዓመታዊ የአባልነት $60 (ስልሳ ዶላር) በድምሩ $200 (ሁለት መቶ ዶላር) እስከ ኤፕሪል 5 ቀን 2023 ዓ ም ድረስ ከፍሎ በማጠናቀቅ ሙሉ አባል መሆን ይጠበቅበታል።
አመልካቾች እሰከ ነገ ማርች 21 ቀን 2023 ዓ ም ድርስ ከፍያውን የሚመለከት የፅሁፍ እና የኢሜይል መልዕክት ይደርሳቸዋል። ይህን መልእክት በመከተል አመልካቾች ከማርች 21 እስከ ኤፕሪል 5 ቀን 2023 ዓ ም ባለው ጊዜ ውስጥ ክፍያቸውን ማጠናቀቅ ይጠበቅባቸዋል። ከኤፕሪል 5 ቀን 2023 ዓ ም በኋላ ዘግይተው የሚከፍሉ
አመልካቾች ተጨማሪ የቅጣት ክፍያ መክፈል ይጠበቅባችዋል።
የኅብረት መረዳጃ ማህበር ሙሉ አባል ለመሆን ይህንን ክፍያ በወቅቱ ማጠናቀቅና የማህበሩን የአባልነት የምስክር ወረቀት ማግኘት አስፈላጊ ነው። ክፍያውን አጠናቆ የማህበሩን የአባልነት የምስክርነት ያላገኘ አመልካች የማህበሩ አባል እንዳልሆነና ምንም አይነት ጥቅም ከማህበሩ እንደማያገኝ አጥብቀን እናሳውቃለን።
በተጨማሪም ዘግይተው የተመዘገቡና የውክልና ቅጹን ዘግይተው የላኩ አመልካቾች በተስማሙት መሰረት ተጨማሪ የቅጣት ክፍያውንም ጨምረው ማጠናቀቅ ይጠበቅባቸዋል።
ማሳሰቢያ

ኅብረት መረዳጃ ማህበር ሥራውን ለመጀመር የሚችለው ማህበሩ ቢያንስ ከ800 አመልካቾች የተጠየቀውን $200.00 የአሜሪካ ዶላር መሰብሰብ ከቻለ ብቻ ነው። ክፍያውን ቢያንስ 800 አመልካቾች ካላጠናቀቁ ኅብረት መረዳጃ ሰራ
የሚጀምርበትን ቀን ወደፊት ለመግፋት ይገደዳል። ካሰፈለገም አዲስ ተመዝጋቢዎችን ለመቀበል ይገደዳል። ይህ ሁሉ እስኪጠናቀቅ ድረስ ማህበሩ ምንም አይነት የሞት ክፍያ ለመክፈል እንደማይችል አጥብቀን እናሳውቃለን።

ለተጨማሪ መረጃዎች የማህበሩ ድረ ገጽ መመልከት ይቻላል።

የኅብረት አስተዳደር ቦርድ

Mail your Payments To: HMAS, PO Box 8487, Silver Spring, MD 20907