September 4, 2022, Robocall Message 

September 4, 2022

ለኅብረት መረዳጃ ማህበር አመልካቾች September 4, 2022

የኅብረት መረዳጃ ማህበር ስራውን ለመጀመር የሚያስችሉትን ቅድመ ዝግጅቶች ሁሉ አጠናቆ በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ይገኛል። ሰለሆነም

በአሁኑ ወቅት ማህበሩ ሥራውን ለመጀመር የአባልነት ምዝገባውን laጠናቀቁ 1208 አመልካቾች የአባልነት መመዝገቢያና አመታዊ ስራ
ማስኬጃ የአንድ ጊዜ መዋጮ መሰብሰብ ይጠበቅበታል።ማህበሩ ባከናወነው ዝርዝር ጥናት መሠረት እያንዳንዱ አባል ለአንድ ጊዜ ብቻ
$00 የአሜሪካን ብር ማዋጣት እንዳለበት አረጋግጧል። ይህ የአንድ ጊዜ መዋጮ ለማህበሩ ስራ ማስጀመርያና ዓመታዊ ስራ ማካሄጃ
የሚውል ይሆናል።

ክፍያውን እስከ ሴምቴበር (September) 26,2022 ዓ.ም ድረስ ለማህበሩ መድረስ ያለበት ሲሆን በቼክና ፣ በክሬዲት ካርድ ሊከናወን
ይችላል: አመልካቾች ወደ ኅብረት ድረገጽ (Hebret.ORG) በመሄድ ፖርታላቸው ውስጥ ገብተው ክፍያውን እንዲፈጽሙ ማህበሩ ያበረታታል
። ስለሆነም ማህበሩ ስራውን ለመጀመር ይችል ዘንድ የአንድ ጊዜ መዋጮውን በተሠጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ እንድትከፍሉ በጥብቅ
እናሳስባለን፡: በተሰጠው የጊዜ ገደብ ክፍያውን የማያጠናቅቁ አመልካቾች የማህበሩ አባል የማይሆኑ መሆኑንም እናስታውቃለን።

ለምዝገባ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ የውክልና ቅጽን አሟልታችሁ ባለማቅረባችሁ እና ዘግይታችሁ ለተመዘገባችሁ አመልካቾች የተወሰነባችሁን
የቅጣት ገንዘብ እንድትከፍሉ የሚጠይቅ ተጨማሪ የክፈሉ መልዕከት ይደርሳችኋል። ክፍያውን ለሚያጠናቅቁ አመልካቾች ብቻ የአባልነት መታወቂያ ካርድ የሚሰጥ መሆኑንም እናስታውቃለን።
ማሳሰቢያ፡

ማህበሩ ሥራውን ለመጀመር ይህ መልዕክት የደረሳችሁ አመልካቾች በሙሉ ክፍያውን በተወሰነለት ጊዜ መሰብሰብ ካልትቻለ ማህበሩ
ስራ ለመጀመር አዲስ አባላትን መዝግቦ ቁጥሩን ማሟላት ወይንም ሌላ አማርጮችን ማጥናት ስለሚኖርበት የሥራ መጀመርያው ጊዜውም
በዚሁ መጠን የሚራዘም መሆኑን እናስገነዝባለን።
ማህበሩ ከላይ የተጠቀሱትን ጉዳዮች ተሟልተውለት ስራውን እስከሚጀምር ድረስ ምንም አይነት የሞት ክፍያ የማያስተናግድ መሆኑን
እናስታውቃለን።

የህብረት መረዳጃ ማህበር ጊዜያዊ አስተዳደር

 

September 10, 2022

ሕብረት የመረዳጃ ማኅበር ስራውን ሙሉ ለሙሉ ለመጀመር ከሚያስፈልጉት ተግባራት አንዱ የማኅበሩን
አመራር (ቦርድ) ማስመረጥ ነው። ይህንን ተግባር ለማከናወን ጊዜያዊ አመራሩ ከእናንተ ከማህበሩ
አመለካቾች በደረሰው ጥቆማ ፣ እንዲሁም ከአሸጋጋሪው ኮሚቴ በተሰጠው ሃላፊነት መሠረት ፣
የአስመራጭ ኮሚቴ አባል ለመሆን የሚያስችሉትን መስፈርቶችን ያሟሉ 5 አመልካቾች የኅብረት
መረዳጃ ማሕበርን ቦርድ እንዲያስመርጡ ሃላፊነት ተሰጥቷቸው ስራ ጀምረዋል።
በተጨማሪም ይህ አዲስ የተዋቀረው አስመራጭ ኮሚቴ ተሰብስቦ ከዚህ በታች እንደተዘረዘረው የስራ
ክፍፍል አድርጓል።
1) ወ/ሮ ኤልሳቤት ወሰን ሊቀመንበር
2) ወ/ሮ ሄርሜላ ከበደ ጸሃፊ
3) ዶ/ር ፍሰሓ እሸቱ አባል
4) አቶ አንተነህ ጥሩሰው አባል
5) አቶ ነጋቱ ጥላሁን አባል
የምርጫ ኮሚቴ ሃላፊነቶች
 ከጊዜያዊ አስተዳደሩ የቀረበለትን የምርጫ ኮሚቴውን የሰራ መመሪያዎች መተግበር
 የምርጫውን የጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀት
 ምርጫውን እስከ ህዳር (November) 30 ቀን 2022 ዓ.ም ማጠናቀቅ
 ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ወደ አዲስ የተመረጠው ቦርድ የሚደረገውን የስልጣን ሽግግር መምራትና በስራ
ላይ ማዋል ናቸው።
ማሳሰቢያ
በቅርቡ አዲስ የተዘጋጀው የማሕበራችን መተዳደሪያ ደንብም ከአመልካቾች የተሰበሰቡትን አስተያየቶች
አካቶ ለመጨረሻ ጊዜ በማህበሩ ጠበቃ እየተገመገመ ይገኛል። የጠበቃው ግምገማ እንደተጠናቀቀ
ምዝገባ ያጠናቀቁ ተመዝጋቢዎች እንዲያጸድቁት ይቀርባል። አዲሱ የቦርድ አባላት ከተመረጡ በኋላ
የማሕበሩ ስራ የሚከናወነው የመተዳደሪያ ድንቡ ላይ በሰፈሩት አንቀጾች ነው።
ስራችንን አጠናቀን ማሕበሩ ስራውን በታቀደው ጊዜ እንዲጀምር አባላት ሁሉ ከአስመራጭ ኮሚቴው
የሚሰጡትን መመሪያዎች እንዲከታተሉና የተጠየቁትን እንዲፈጽሙና የማሕበሩንም የውስጥ
መተዳደሪያ በሚሰጠው የጊዜ ገደብ እንዲያጸድቁ እናሳስባለን።
አዲሱ አስተዳደር ስራ እስከሚጀምር ድረስ የኅብረት ጊዜያዊ አስተዳደር ምንም አይነት የሞት ክፍያ
ጥያቄ ለመቀበልና ለማስተናገድ እንደማይችል በጥብቅ እናሳውቃለን።