ተደጋግሞ የሚነሱ ጥያቄዎች / Frequently Asked Questions

How to use the Portal – Video

1.ፖርታ ውስጥ እንዴት መግባት እችላለሁ? ምዝገባውን እንዳጠናቀቁ ከኅብረት መረዳጃ አይቲ ቲም የፖርታል አገናኝ ሊንክ ያለው ኢሜል ባስመዘገቡት የኢሜል አድራሻ ይደርስዎታል፡፡ ወደ ፓርታሉ ለመግባት ሊንኩን ተጭነው የይለፍ ፓስወርድ ይፍጠሩ፡፡ (የይለፍ ፓስወርድዎትን በማስታወሻዎት ይመዝግቡት፡፡)

 How do I access Hebret Portal on the website? Upon completion of the registration, you will receive an email from Hebret IT team a portal link. Click the link to create the password to access the Portal then it will let you into the system. 

2.  ወደ ፖርታሉ መግቢያ ጥሪውን ሳልቀበል ፖስወርድ መፍጠር ይቻላል? አይቻልም። ፓስወርድ መፍጠር የሚቻለው ወደ ፖርታሉ የሚያስገባውን የጥሪ ሊንክ መጀመሪያ ሲጫኑ ብቻ ነው።

Can I create a password without accepting the Portal access invitation? No, you cannot. You only can create your password after you accept the Portal access invitation.

3. ፖርታል ወስጥ መግቢያው ሊንክ ካልደረሰኝ ምን ላድርግ? ወደ ፖርታል መግቢያ ሊንኩን ካላገኙት ወደ አላስፈላጊ ኢሜል ስፓም (SPAM) ወይንም ጃንክ (JUNK) ኢሜል ውስጥ ገብተው ይፈልጉት። ካላገኙት ወደ ኅብረት ኢሜል hebret2021@hebret.org ጥያቀዎን ይላኩ ወይንም በ (703) 455-0236 ይደውሉ እንረዳዎታለን።

What if I can’t find the Portal access invitation link? If you can’t find the link in your email, search for it in your SPAM or JUNK emails. If you still can’t find email Hebret for support. Please send an email to hebret2021@hebret.org or call the customer’s support desk (703) 455-0236

4. ፖርታል ውስጥ ለመግባት አንድ ኢሜል አድራሻ ለሁለት አባሎች መጠቀም ይቻላል? ካልተቻለ ምን ላድርግ? አይቻልም። ፖርታሉ ውስጥ ለመገባት እያንዳንዱ አባል የራሱ የሆነ ኢሜል አድራሻ እንዲኖረው ግዴታ ነው። ይህ ካልሆነ ፖርታል ውስት የሚገባው ከሁለት አንዱ ብቻ ነው። ስለዝህ ሁለተኛ ኢሜል አድራሻ መፍጠር ወይንም ሌላ ሁለተኛ ኢሜል መጠቀም አለቦት።

Can two family members use one email address to access the Portal? If not, what can I do? No, you can’t. Each member should have one email address of their own. If not, only one member can access the Portal. In this case, you must create a new password or use another password.

5. ኖተራይዝድ የተደረገውን የውክልና ደብዳቤ እንዴት መላክ እችላለሁ?
ኖተራይዝድ የተደረገውን የውክልና ደብዳቤ በፖስታ ቤት አድራሻችን 7961 Eastern Avenue Suite # 301 Silver Spring, Md 20910 በኩል መላክ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን የኅብረት አመራር አባላት መዘግየትን ወይም ጉድለቶችን ለማስቀረት ኦንላይን ሲስተም እንዲጠቀሙ ያበረታታል፡፡ ኖተራይዝድ ሰነዱን በኢሜይል አድራሻችን hmas2021@hebret.org ወይንም የአባል ፖርታል ላይ መጫን ይችላሉ።
How can I send the notarized Individual Designee Form?
You can mail it to Hebret address 7961 Eastern Avenue Silver Spring Md 20910 thru the post office, but the Hebert management is recommending that members use the online system to avoid delay or mishaps/omissions. The scanned notarized document can be uploaded directly into the member’s portal system or send email to hmas2021@hebret.org

6. ኖተራይዝድ የተደረገውን የውክልና ደብዳቤ በተመደበለት ቀን ውስጥ ባይደርስ ምን እርምጃ ይወሰዳል?
የውክልና ፎርሙ ኖተራይዝድ ተደርጎ በተመደበለት ቀን ውስጥ ካልደረሰ ተመዝጋቢው ለአባለነት የሚያስፈልገውን ቅጽ ስላላሟሉ ከአባልነት ይሰረዛሉ።.

What action will be taken if the notarized letter is not received within the allocated time?
The registrar is not considered as a member and will not qualify for membership and will be canceled.

7. አንድ አባል ሙሉ ጥቅም ማግኘት የሚጀምረው መቼ ነው?
ማመልከቻውና የውክልና ደብዳቤው ታየቶ ተቀባይነት ካገኘና ሁሉም የአባልነት ክፍያ ሙሉ በሙሉ ከተከፈለ በኋላ አመልካች አባል ሆኖ ይቆጠራል የአባልነት መታወቂያም ይሰጠዋል። ክፍያ የሚከናወነው ማህበሩ ሙሉ ሥራውን ከጀመረ በኋላ ነው። ማህበሩ ስራ የሚጀምርበትን ቀን ለአባላቱ አስቀድሞ ይፋ ያደርጋል።
When does a member entitled to full benefit?
After the application and the Designee letter (Notarized letter) have been approved and all membership fees have been paid in full, the applicant will be considered a member of Hebret and a membership ID will be issued. Benefit payment takes place only after the Society launches its full operation. A “Start Date” will be announced to members ahead of time.

8. ኅብረት ስራውን የሚጀምረው መቼ ነው?
ድርጅቱ ሰራ ለመጀመር የሚያስፈልጉትን መስፈርቶችን አሟልቶ እንዳጠናቀቀ የማህበሩ የአገልግሎት መጀመሪያ ቀን ለአባላቱ ያሳውቃል።
When does Hebret begin operation?
Announces the opening day of the association as soon as Hebret has met all the requirements to commence or start its work.

9. የኅብረት ቢሮ/አድራሻ የሚገኘው የት ነው? ስልክ ቁጥሩስ?
ኅብረት በሲልቨር ስፕሪንግ ሜሪላንድ መሃል ከተማ ላይ ይገኛል። ቢሮው ቅዳሜ ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ 10 ሰዓት ከፍት ነው
አድራሻው 7961 Eastern Avenue Suite # 301 Silver Spring, Md 20910
ስልክ ቁጥር (240)-641-4917)
Where is the office located? What is the phone number?
Hebret is in downtown Silver Spring Maryland. The office is open on Saturday’s 10 AM to 4 PM.
The address is 7961 Eastern Avenue Silver Spring Md 20910
TEL (240)-641-4917