October 9, 2022

ሕብረት የመረዳጃ ማኅበር ስራውን ሙሉ ለሙሉ ለመጀመር ከሚያስፈልጉት ተግባራት አንዱ የማኅበሩን
አመራር (ቦርድ) ማስመረጥ ነው። ይህንን ተግባር ለማከናወን ጊዜያዊ አመራሩ ከእናንተ ከማህበሩ
አመለካቾች በደረሰው ጥቆማ ፣ እንዲሁም ከአሸጋጋሪው ኮሚቴ በተሰጠው ሃላፊነት መሠረት ፣
የአስመራጭ ኮሚቴ አባል ለመሆን የሚያስችሉትን መስፈርቶችን ያሟሉ 5 አመልካቾች የኅብረት
መረዳጃ ማሕበርን ቦርድ እንዲያስመርጡ ሃላፊነት ተሰጥቷቸው ስራ ጀምረዋል።
በተጨማሪም ይህ አዲስ የተዋቀረው አስመራጭ ኮሚቴ ተሰብስቦ ከዚህ በታች እንደተዘረዘረው የስራ
ክፍፍል አድርጓል።
1) ወ/ሮ ኤልሳቤት ወሰን ሊቀመንበር
2) ወ/ሮ ሄርሜላ ከበደ ጸሃፊ
3) ዶ/ር ፍሰሓ እሸቱ አባል
4) አቶ አንተነህ ጥሩሰው አባል
5) አቶ ነጋቱ ጥላሁን አባል
የምርጫ ኮሚቴ ሃላፊነቶች
 ከጊዜያዊ አስተዳደሩ የቀረበለትን የምርጫ ኮሚቴውን የሰራ መመሪያዎች መተግበር
 የምርጫውን የጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀት
 ምርጫውን እስከ ህዳር (November) 30 ቀን 2022 ዓ.ም ማጠናቀቅ
 ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ወደ አዲስ የተመረጠው ቦርድ የሚደረገውን የስልጣን ሽግግር መምራትና በስራ
ላይ ማዋል ናቸው።
ማሳሰቢያ
በቅርቡ አዲስ የተዘጋጀው የማሕበራችን መተዳደሪያ ደንብም ከአመልካቾች የተሰበሰቡትን አስተያየቶች
አካቶ ለመጨረሻ ጊዜ በማህበሩ ጠበቃ እየተገመገመ ይገኛል። የጠበቃው ግምገማ እንደተጠናቀቀ
ምዝገባ ያጠናቀቁ ተመዝጋቢዎች እንዲያጸድቁት ይቀርባል። አዲሱ የቦርድ አባላት ከተመረጡ በኋላ
የማሕበሩ ስራ የሚከናወነው የመተዳደሪያ ድንቡ ላይ በሰፈሩት አንቀጾች ነው።
ስራችንን አጠናቀን ማሕበሩ ስራውን በታቀደው ጊዜ እንዲጀምር አባላት ሁሉ ከአስመራጭ ኮሚቴው
የሚሰጡትን መመሪያዎች እንዲከታተሉና የተጠየቁትን እንዲፈጽሙና የማሕበሩንም የውስጥ
መተዳደሪያ በሚሰጠው የጊዜ ገደብ እንዲያጸድቁ እናሳስባለን።
አዲሱ አስተዳደር ስራ እስከሚጀምር ድረስ የኅብረት ጊዜያዊ አስተዳደር ምንም አይነት የሞት ክፍያ
ጥያቄ ለመቀበልና ለማስተናገድ እንደማይችል በጥብቅ እናሳውቃለን።