• Financial Reports and Audit Reports

  • ጤና ይስጥልኝ
    የኅብረት መረዳጃ ማህበር ለጠቅላላ ጉባኤ ሰብሰባ ጥሪያችንን አክብራችሁ ለተገኛችሁ እጩ አባላት እንኳን
    በደህና መጣችሁ። እኔ ጣይቱ አማረ እባላለሁ የጊዜያዊ አስተዳድሩ ሊቀመንበር ነኝ፤ ከዚህ በታች
    ስማቸው የተዘረዘሩት የጊዜያዊ አስተዳደሩ አባላት
    ወ/ሮ ታፈሰወርቅ ገበየሁ ጸሓፊ
    አቶ በላይሁን አስረስ ገንዘብ ያዝ
    ወ/ሮ ፈሊሺያ በቀለ አባል
    ዶክተር ሰለሞን አለሙ አባል
    እንዲሁም መሃበራችን አስፈላጊውን ዕርዳታ በጠየቀበት ቦታ ሁሉ እየገቡ አስተዋጽዋቸውን ሲያደርጉ
    ለነበሩ ከጊዜያዊ አስተዳረሩ ጋር አብረው የተጓዙትን የሽግግር ግብረ ሃይል (Transition Team) አባላት
    በሙሉ ማህበራችንን ጊዜያቸውን ሰውተው በፈቃደኝነት ኅብረሰብን ለማገልገል የድርሻቸውን በመወጣት እሰከ
    አሁን ላደረጉት ተሳትፎ በዕጩ አባላት ሰም ሆኜ አክብሮቴንና ምስጋናዪን ማቅረብ እፈልጋለሁ።
    በመቀጠልም ጊዜያዊ አስተዳደሩን ወክዪ የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ ለማሳለፍ ድምፅ በመስጠት
    የተሳተፋችሁትን ዕጩ አባላት በሙሉ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።
    የዛሬ ስብሰባችን የሚያተኩረውና ልንወያይባቸው ያቀደናቸው ሦስት ርዕሰ ጉዳዮች አሉን ። እነዚህም፤
    1ኛ አጠቃላይ የማህበሩ ሪፖርት
    2ኛ የፋይናንስ ሪፖርት
    3ኛ የወደፊት የማኅበሩ የሰራ አቅጣጫ ናቸው
    እንደሚታወቀው የህብረት ጊዜያዊ አስተዳደር ከመቋቋሙ ቀደም ብሎ “በሁሉም ለአንድ ማህበር” ጠቅላላ
    ጉባኤ ተቋቁሞ የነበረው የችግር አስወጋጅ ግብረ ሃይል (Task Force) በተሰጠው መመሪያ መሠረት
    አሸጋጋሪ ቡድን (Transition Team) በማቋቋምና በአንድነት በመሥራት በርካታ ተግባራትን አከናውኗል፤
    ከእነዚህም መካከል ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል
    የሚቋቁመው ድርጅት ምን መልክ እንደሚኖረውና የትኛው ስቴት እንደሚመሠረት ጥናት አካሄዶ በሜሪላድ
    ሕጋዊ ሰውነት እንዲያገኝ አድርገዋል.
    • ከ Maryland State እና ከ IRS ሕጋዊ ሴርቲፊኬቶችን አውጥቷል
    • ለድርጅቱ የሕግ አማካሪ በመቅጠር የማህበሩ እንቅስቃሴ ሕግን የተከተለ መሆኑን አረጋግጠዋል
    • የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ ረቂቅ አዘጋጅቷል.
    • ጊዜያዊ አስተዳደሩን December 17 2021, ካስጸደቀ በኋላ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ከ December 19
    ቀን 2021 ዓ.ም. ጀመሮ ኃላፊነትን ተረክቦ በመሥራት ላይ ይገኛልጊዜያዊ አስተዳደሩ ከተሰጡት ኃላፊነቶች
  • መሃል ዋነኛው አዲሱን የኅብረት መረዳጃ ማኅበርን ማቁቋም፤
    መተዳደሪያ ደንቡን ማጠናቀቅና ማስጸደቅ፤ አስመራጭ ኮሚቴውን ማስመረጥ ቋሚ ቦርዱንና የመማከርት
    አባላትን አስመርጦ ጊዜያዊ አመራሩ የስራ ሽግግር እንዲያደርግ ነው።
    ይህንንም ሃላፊነት ለመወጣት፣ ከዕለት ዕለት መሰራት ከሚገባቸው ስራዎች በተጨማሪ የሚከተሉትን
    አበይት ስራዎች አከናውኗል።
    1ኛ – የማኅበሩን ጽህፈት ቤት በመሃል ሲልቨር ስፕሪንግ ከተማ ተከራየ፤ የማኅበሩን የባንክ አካውንት
    ከፈተ፣ የኅብረትን አርማ እንዲሁም፣ ድህረ ገጽ ገንብቶ በሳራ ላይ አውሏል
    2ኛ – 1209 እጩ አባላትን መዝግቧል። ምዝገባ ሰንል የሰው ስም መመዝገብ ብቻ ሳይሆን ፣ እያንዳንዱ
    አባል ፎርሙን በትክክል መሞላቱን ማረጋገጥ፣ እጩ አባላት ሕጋዊ ወኪል ሰይመው ኖተራዝ በማስደረግ
    እንዲያሳውቁ፤ ከዚያም ያልተሟሉ ፎርሞች ካሉ እያንዳንዱ እጩ አባል ጋር መደወል፣ ለእያንዳንዱ እጩ
    አባል ኢሜል መላክ፣ ጥያቄ ያላቸውን እንዲሁም ፎርሙን ብቻቸውን መሙላት የማይችሉ ወገኖቻችንንም
    መርዳት ያጠቃልላል። ይህ እጅግ ከፍተኛ ጊዜ ወስዷል።
    3ኛ – የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ አዘጋጅቶ አስጸድቋል። መተዳደሪያ ደንቡን ማስጸደቅ ስንል፣ ከህግ
    ባላሙያዎች ጋር በተደጋጋሚ መወያየት፤ ከአባላት አስተያየቶችን መሰብሰብና የመጨረሻውን ሰነድ
    ማዘጋጀትና ለድምጽ ማዘጋጀትን ያጠቃልላል።
    4ኛ – የውስጥ የገንዘብ አያያዝ፤ የስራ ቅደም ተከተል የሚተነትን ብዙ ጉልበት የፈሰሰበትን መሠረታዊ
    ሰነድ ማዘጋጀትን የመሳሰሉትን እጅግ በርካታ ስራዎችን ለማከናወን ተችሏል።
    እነዚህ ሁሉ ስራዎች ሲከናወኑ ብዙ ችግሮችና ተግዳሮቶች እንደገጠሙንም ልገልጽላችሁ እወዳለሁ።
    የአባላትን ምዝገባ በታሰበው ጊዜ ውስጥ መጨረስ አልቻልንም። የዚህም ዋናው ምክንያት፣
    እጩ አባላት በተላለፈው መመሪያ መሰረት በተሰጠው ጊዜ ፎርሞችን በትክክል ለመሙላት ያለመቻላቸው
    ነው። ስለዚህም እጅግ ብዙ መልእክቶች በሮቦ ኮል፣ በኢሜልና በቴክስት እንድናደርግና ለሊት ቁጭ ብለን
    ፎርሞቹን ስናስተካክል እንድናድር አስገድዶናል። በዚህ ምክንያት የምዝገባውን ጊዜ በተደጋጋሚ
    አራዝመናል።
    በመጭረሻም በዙ የሰልክ ጥሪዎች ይመጣሉ ነገር ግን 90% የሚሆኑት ደዋዮች ሰማቸውንና ጥያቂያቸውን
    ሳይናገሩ መልሳችሁ ደውሉ በማለት መልዕክት ይተዋሉ ነገር ግን ግልጽ መልዕክት ካላገኘን በትርፍ ጊዜ
    ለሚሰራ ሰራ በጊዜ መልሶ ለመደወል ያሰቸገራል። ይህንን ችግር ለመቅረፍ ወደፊት ማሀበሩ ሲጠናከርና
    አስፈላጊ ሆኖ ሰገኘ ቢሮ ውስጥ የሚቀመጥ ጸሃፊ የቀጥራል። እስከዛው መልዕት ሰትተዉ ሰማችሁን
    ሰልካችሁን እንዲሁም ጥያቀአችሁን ባጭሩ እንድታስቀምጡ እናሳሰባለን።
    አሁንም ይህ ማኅበር እንዲጠናከርና እድሜው እንዲረዝም ሁላችንም መተባበርና በፈቃደኝነት ለመስራት
    ቆርጠን መነሳት አለብን። የዚህን ማህበር ስራ ጥቂት ሰዎች ትከሻ ላይ የምንጥል ከሆነ፣ የማኅበሩን ህልውና
    አደጋ ላይ እንደምንጥል መረዳት አለብን።
    ለእጩ አባላት አስረግጬ ለመግለጽ የምፈልገው ይህንን ሥራ የሚሠሩ ግለሰቦች ያለአንዳች ክፍያ
    በፈቃደኝነት ብቻ የምንለፉና እንደ ብዝዎቻችሁ መደበኛ ሥራ የምንሰራ ሰዎች መሆናችንን ነው።
  • ከዚህ ቀጥሎ አቶ በላይሁን አስረስ የሂሳብ ሪፖርት ያቀርብልናልክቡራትና ክቡራን፡
    ከብዙ ውጣ ወረድ በኋላ ዛሬ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ማኅበራችን ስራውን የሚጀምርበት ጊዜ እየተቃረበ
    ነው። ይህንኑ በማሰብ የውስጥ መተዳደሪያችንን እያዘጋጀንና መተዳደሪያ ደንቡን ለማስጸደቅ ዝግጅት
    እያረግን በተጓዳኝ የማኅበሩን ቦርድ አቋቁመን ስራችንን እናጠናቅቃለን ብለን በእናንተ ጥቆማ September
    8/2022 አስመራጭ ኮሚቴ ተቋቋመ። በነበረን እቅድ መሠረት ምርጫው Nov30, 2022 እንዲጠናቀቅ
    ሃላፊነቱን ለአስመራጭ ኮሚቴው ሰጠን።
    ይሁን እንጂ አስመራጭ ኮሚቴው በእነዚህ ሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ ምንም እርምጃ ለመውሰድ
    ባለመቻሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ ስራችንን እንጀምራለን የሚለው ምኞታችንም እውን ሊሆን እንደማይችል
    ተረዳን።
    ካገኘነው ልምድ በመነሳት ለተቋቋመው ኮሚቴ ተጨማሪ ጊዜ መስጠትም ሆነ ሌላ ኮሚቴ ማቋቋም
    የማህበሩን ሥራ መጀመር እጅግ ስለሚያስረዝም ሌሎች አምርጮችን ለመፈለግ ተገደድን። የተለያዩ
    አማራጮችን ከመረመርን በኋላ ማኅበሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ ስራውን እንዲጀምር ከዚህ በታች ያለውን
    ሃሳብ ለውሳኔ አቅርበናል.
    ለሚቀጥሉት አራት አመታት ማሕበሩን የሚመሩ የቦርድ አባላትና የመማክርት ጉባኤ በቀጥታ የመምረጥና
    የመሰየም ሃላፊነት ለጊዜያዊ አመራር እንዲሰጠው እንጠይቃለን።
    ይህ ሃሳብ ሲብራራ ይህን ይመስላል።
    1ኛ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ድርጅቱን የሚመሩ የቦርድና የመማክርት (ገቨርኒንግ ካውንስል) አባላትን
    ጊዜያዊ አመራሩ ይመለምላል።
    2ኛ – በተቻለ መጠን የሚመረጡት አባላት በእውቀታቸውና ስነ ምግባራቸው የማኅበሩን አላማና ግብ
    የሚመጥኑ መሆናቸውን ያረጋገጣል
    3ኛ – የተመረጡትን አመራር አባላት ለዕጩ አባላት በድረ ገጻችንና በሮቦ ኮል እናሳውቃለን
    4ኛ – ስራውን ከተረከቡ በኋላ ስራቸውን በአግባቡ እንዲጀምሩ የአሰራር ልምዳችንን በማካፈል
    አብሯቸው ይሰራል።
    ከላይ ያቀረብነውን ሃሳብ እንድታጸድቁልን በማክበር እየጠየኩ ንግግሬን ስላዳመጣችሁኝ ምስጋናዬን
    አቀርባለሁ። 
  • General assembly Financial Report
  • AFOA Audit Report

Home Page

Hebret Mutual Aid Society -ኅብረት መረዳጃ ማህበር

7961 Eastern Ave NW Ste# 301, Silver Spring, MD 20910–Email: Hebret2021@gmail.com