Jun 26, 2022
ለኅብረት መረዳጃ ማህበር ተመዝጋቢዎች
ማሳሰቢያ ከቀድሞ የሁሉም ለአንድ ማህበር ወደ ኅብረት መረዳጃ ማህበር:

መመዝገቢያ ጊዜ ላሳለፉ አመልካቾች የኅብረት መረዳጃ ማኅበርን ስራ ለመጀመር ከሚያስፈልጉት ዋና ዋና ክንውኖች መሃል አንዱ የአባላት ምዝገባ ሂደትን ማጠናቀቅ ነው። ሁላችሁም እንደምታውቁት የአባልነት ማመልከቻ የምዝገባ ሂደቱ ከኤፕሪል ( (April 11, 2022) እስከ ሜይ (May) 11 2022 ባለው ጊዜ ተካሂዶ ተጠናቋል።

ነገር ግን በህመም ምክንያት ወይንም ከአገር ውጭ ለሆኑ ለቀድሞው የሁሉም ለአንድ ማኅበር የአባላት ምዝገባ ከተጅመረ ጀምሮ ለ90 ቀናት የተራዘመ መሆኑንና እስከ ጅላይ (July) 11 ቀን 2022 መመዝገብ እንደሚቻል አሳውቀናል። ይህንን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች በሙሉ ምዝገባውን ከመዝጋታችን በፊት የሚከተሉትን አሟልቷችሁ እንድትልኩ በትህትና እናሳስባለን፡፡

1ኛ አባላት የህክምና ወይንም የመግቢያ ቪዛ ወይም የጉዞ ትኬት መረጃዎቻቸውን በኅብረት ኢሜል አድራሻችን HMAS2021@HEBRET.ORG በአስቸኳይ መላክ ይጠበቅባኋል፡፡
2ኛ ኅብረት ጊዜያዊ አስተዳደር የቀረቡትን መረጃዎች በጥንቃቄ ካየና ካጸደቀ በኋላ የመመዝገቢያ ቅጹን በኢሜል እንዲደርሳችሁ ያደርጋል።

ስለሆነም ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች ብቻ መመዝገብ ያልቻላችሁ የቀድሞ የሁሉም ለአንድ ማህበር አባላት መመዝገብ የምትችሉበት የጊዜ ገደብ የሚጠናቀቀው ጅላይ (July) 11 ቀን 2022 ዓ.ም እንደሆነ በጥብቅ እናሳስባለን።

ይህ የምዝገባ ማረጋገጫ ሂደት ለወደፊት እርምጃችንና ማህበሩ በአፋጣኝ ስራውን እንዲጀምር ወሳኝ ስለሆነ፣ አባላት ትኩትረ ሰጥተውት የምዝገባ ቀን ሳይዘጋ በፍጥነት ምዝገባውን እንዲያጠናቅቁ አጥብቀን ማስገንዘብ እንወዳለን።

ኅብረት መረዳጃ ማኅበር ጊዜያዊ አመራር
Our Mailing Address is:
Hebret Mutual Aid Society, Inc,
7961 Eastern Ave, Suite 301, Silver Spring, MD 20910
Email: HMAS2021@hebret.org
Tel: (240) 641-4917 Customer Service : 703 455-0236
Our office is open only on Saturday from 10:00 AM to 4:00 PM

——————————————————————

Jun 23, 2022

ለኅብረት መረዳጃ ማህበር ተመዝጋቢዎች

ይህ መልዕክት በተደጋጋሚ በርከት ያሉ ማሳሳቢያ ተልኮላቸው የአባልነት መመዝገቢያውን ሞልተው ነገር ግን የውክልና ቅጹን በተሰጠው የጊዜ ገደብም ሆነ በተራዘሙት ቀናት ውስጥ ያላቀረቡ አመልካቾችን ብቻ ይመለከታል።

በተሰጠው የጊዜ ገደብ ፎርሙን ሞልተው ማቅረብ ያልቻሉ አመልካቾች ተጨማሪ ቀን ተሰጥቷቸው ቅጹን ሞልተው ለመላክ እንዲችሉ ጥያቄ አቅርበዋል።

ጊዚያዊ አስተዳደሩ በቂ ጊዜ ከመመደቡ ባሻገር፣ ቀኑን በማራዘም እንደዚሁም በተለያዩ ጊዜያት ተደጋጋሚ ማሳሰቢያና ማስታወሻዎች በኢሜል፣ በቴክስትና በድምጽ ስልክ አስተላልፎ እንደነበረ ይታወሳል። ቅጹን በጊዜ ያለመሙላት፣ ማሕበሩ በጊዜ ስራውን እንዳይጀምር ከፍተኛ ተጽእኖ አሳድሯል። እጅግ በርካታ የሰው ሃይልም ካለአግባብ እንዲባክን አድርጓል። ቢሆንም ግን የሕብረት መረዳጃ ማኅበር ጊዜያዊ አስተዳደር በቀረበለት ጥያቄ ላይ ከተወያየ በኋላ አመልካቾች አንድ የመጨራሻ እድል እንዲያገኙ በማሰብ የሚከተለውን ውሳኔ አሳልፏል።

1. እስከ አሁን ቅጹን ሞልተው ያላቀረቡ አመልካቾች፣ ከ ሰኔ 22፣ 2022 (June 29, 2022) በፊት በኖተሪ የተረጋገጠ (ኖተራይዝድ) የሆነ የተሟላ ቅጽ ማቅረብ ይችላሉ። ኖተራይዝድ ያልሆነና ያልተሟላ እንዲሁም ስርዝ ድልዝ ያለው ቅጽ ተቀባይነት አይኖረውም።

2. ቅጹን hmas2021@hebret.org ኢሜል ብቻ መላክ ይችላሉ።

3. ከአሁን እስከ ሰኔ 22፣ 2022 (June 29, 2022) ቅጹን የሚያስገቡ አመልካቾች፣ ከተሰጠው የጊዜ ገደብ አሳልፈው ስለላኩ፣ $50.00 ብር ቅጣት ይከፍላሉ።

4. የተወሰነው $50.00 ቅጣት ለወደፊት የሚከፈለው የአባልነት መመዝገቢያ ክፍያ ላይ ይጨመራል። የቅጣቱ ክፍያ የሚሰበሰበው ድርጅቱ ስራ ሲጀምር ነው።

5. በህመም ወይንም ከአገር ውጪ በመሆናቸው ቅጹን ማቅረብ ያልቻሉ አመልካቾች በቂ ማስረጃ ማቅረብ ከቻሉ ይህ ቅጣት አይመለከታቸውም።

ኅብረት ጊዜያዊ አስተዳደር

አባላት ፎርሙን ሲሞሉ እክል ካጋጠማቸው፣ በ (240) 641-4917 ወይም በ (703) 455-0236 ደውለው መልዕክት መተው ይችላሉ።
Our Mailing Address is:
Hebret Mutual Aid Society, Inc,
7961 Eastern Ave, Suite 301, Silver Spring, MD 20910
Email: HMAS2021@hebret.org
Tel: (240) 641-4917 Customer Service : 703 455-0236
Our office is open only on Saturday