July 1 , 2022

ማሳሰቢያ
ስለ ውክልና ቅጽ አለማሟላት –
ፎርሙን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ ኅብረት መረዳጃ ማህበር የአመልካቾችን የውክልና ቅጽ የማጥራትና ትክክለኛነቱን የማረጋገጥ ሂደት እያካሄደ ይገኛል። የኅብረት ጊዜያዊ አመራር
የውክልና ቅጹን በጥንቃቄ ከገመገመ በኋላ ከዚህ በታች ያሉትን ጉድለቶች አስፍሯል፤
1ኛ የአንድ ወይም የሁለት ተወካዮች የመጭረሻ 4 ሶሻል ሴኩሪቲ ቁጥር አለመጻፍ
2ኛ በፎርሙ ላይ የተፃፈው የኅብረት መረዳጃ ማኅበር መታውቂያ መሆን ሲገባው የቀድሞ የሁሉም ለአንድ ማኅበር መታወቂያ ቁጥርን መሙላት
(የሁሉም ለአንድ ማኅበር የፈረሰና በመንግስት የተዘጋ መሆኑ ይታወቃል)
3ኛ የአንድ ወይም የሁለት ተወካዮች የመታወቂያ ቁጥር ማለትም የመንጃ ፈቃድ ወይንም ፓስፖርት ቁጥር፤ የመኖሪያ አድራሻቸውን፤ የኢይሜል አደራሻና የቤት ወይም የእጅ ሰልክ ቁጥር ባዶ መተው ወይንም አለመጻፍ
4ኛ ከተፈረመና ኖተራይዝድ ከሆነ በኋላ ቅጽ ላይ የጎደለውን መረጃ በመጻፍ ወይ ሰርዞ ደልዞ ቅጽ ላይ በመጻፍ ለኅብረት መልሶ በመላክ ጊዜያዊ አስተዳደሩ በኢሜል አማካኝነት ስህተቶቹን ለማስተካከል እያንዳንዳችሁን ለማነጋገር ሞክሮ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህንን በአጥጋቢ መልኩ ማሳካት አልቻልንም። በዚህ አጋጣሚ መግለጥ የምንወደው ቅጹን ያለማስተካከል፣ ማሕበሩ በጊዜ ስራውን እንዳይጀምር ከፍተኛ ተጽእኖ ማሳደሩንና እጅግ በርካታ የሰው ሃይልም ካለአግባብ እንዲባክን ማድረጉን ነው፡፡

የውክልና ቅጹ ከተፈረመና ኖተራይዝድ ከሆነ በኋላ ሰርዞ ደልዞ መጻፍ ህጋዊነት የለውም። ሰለሆነም ይህ መልዕክት የደረሳችሁ አመልካቾች ሁሉ በአዲስ ፎርም የትኛውንም ቅጽ ባዶውን ሳይተዉ መረጃዎችን አሟልታችሁ ኖተራይዝድ አስደርጋችሁ በኢሜል አድራሻችን
HMAS2021@HEBRET.ORG እስከ July 7, 2022 በአስቸኳይ ኢሜል እንድትልኩልን እናሳስባለን።

በተጨማሪም ቢሮአችን የፊታችን ቅዳሜ ሓምሌ (July) 1 ከጠዋቱ 4 ሰዓት (10 AM) እስከ 10 ሰዓት (4 PM) የምንከፍት መሆኑን እያበስርን የውክልና ቅጹን በመሙላትና ኖታሪ አስደርጋችሁ በቢሮ ተገኝታችሁ ማስገባት እንደምትችሉ ልንገልጽ እንወዳለን፡፡

የውክልና ቅጽን ተስተካክሎ እስከ July 7, 2022, ካልደረሰን፣ በተወሰነው ቀን ያስገቡትን የሌላውን አባላት መብት የተጋፋን ሰለመሰለን ኅብረት የአባል ጥያቄዎን ለመሰረዝ እንደምንገደድ በአጽንኦት ለማሳወቅ እንወዳለን።

——————————————————————

ስለ ውክልና የአባል ቁጥር አለማሟላት July 1, 2022

ኅብረት መረዳጃ ማህበር የአመልካቾችን የውክልና ቅጽ የማጥራትና ትክክለኛነቱን የማረጋገጥ ሂደት ውስጥ ነው። የኅብረት ጊዜያዊ አመራር የውክልና ቅጹን በጥንቃቄ ከገመገመ በኋላ ከዚህ በታች ያሉትን ጉድለቶች አስፍሯል፡፡
1ኛ የኅብረት መታወቂያ ቁጥር ሳይሞላ የቀረ ወይንም (የኅብረት መታወቂያ ቁጥር ለማግኘት ፓርታሉ ውስጥ ይግቡ)
2ኛ በፎርሙ ላይ የተፃፈው የቀድሞ የሁሉም ለአንድ መታወቂያ ቁጥር መሞላት
3ኛ ከተፈረመና ኖተራይዝድ ከሆነ በኋላ ቅጹ ላይ የኅብረትን መታወቂያ በመጻፍ
4ኛ ከተፈረመና ኖተራይዝድ ከሆነ በኋላ ቅጹ የቀድሞ የሁሉም ለአንድ መታወቂያ ቁጥሩን በመሰረዝ እና በመደለዝ የኅብረትን ቁጥር በዛው ቅጽ ላይ በመጻፍ መላክ

ጊዜያዊ አስተዳደሩ በኢሜል አማካኝነት ስህተቶቹን ለማስተካከል እያንዳንዳችሁን ለማነጋገር ሞክሮ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህንን በአጥጋቢ መልኩ ማሳካት አልተቻለም። በዚህ አጋጣሚ መግለጥ የምንወደው ቅጹን በትክክል አለመሙላትና በጊዜ ያለማስተካከል፣ ማሕበሩ ስራውን እንዳይጀምር ከፍተኛ ተጽእኖ ማሳደሩንና እጅግ በርካታ የሰው ሃይልም ካለአግባብ እንዲባክን ማድረጉን ነው፡፡

የውክልና ቅጹን ከተፈረመና ኖተራይዝድ ከሆነ በኋላ ሰርዞ ደልዞ መጻፍ ህጋዊነት የለውም። ሰለሆነም ይህ መልዕክት የደረሳችሁ አመልካቾች ሁሉ አዲስ ፎርም ሞልታችሁ ኖተራይዝድ የሆነ የውክልና ቅጽ በኢሜል አድራሻችን HMAS2021@HEBRET.ORG እስከ
July 7, 2022 በአስቸኳይ እንድትልኩልን እናሳስባለን።

በተጨማሪም ቢሮአችን የፊታችን ቅዳሜ ሓምሌ (July) 1 ከጠዋቱ 4 ሰዓት (10 AM ) እስከ 10 ሰዓት (4 PM) የምንከፍት መሆኑን እያበስርን የውክልና ቅጹን በመሙላትና ኖታሪ አስደርጋችሁ በቢሮ ተገኝታችሁ ማስገባት እንደመትችሉ ልንገልጽ እንወዳለን፡፡

የውክልና ቅጹን ተስተካክሎ እስከ July 7, 2022, ካልደረሰን፣ በተወሰነው ቀን ያስገቡትን የሌላውን አባላት መብት የተጋፋን ሰለመሰለን ኅብረት የአባል ጥያቄዎን ለመሰረዝ እንደምንገደድ በአጽንኦት ለማሳወቅ እንወዳለን። (የኅብረት መታወቂያ ቁጥር ለማግኘት ፓርታሉ ውስጥ ይግቡ)

የኅብረት ጊዜያዊ አመራር

Our Mailing Address is:
Hebret Mutual Aid Society, Inc,
7961 Eastern Ave, Suite 301, Silver Spring, MD 20910
Email: HMAS2021@hebret.org
Tel: (240) 641-4917 Customer Service : 703 455-0236
Our office is open only on Saturday from 10:00 AM to 4:00 PM

 


JULY 2 2022

ቀድሞ የሁሉም ለአንድ ማህበር ወደ ኅብረት መረዳጃ ማህበር መመዝገቢያ ጊዜ ላሳለፉ አመልካቾች እንዲሁም ሳይመዘገቡ የውከልና ቅጹን ሞልተው ለላኩ አመልካቾች July 2 2022

July 2, 2022

To download form Click here/ፎርሙን እዚህ በመጫን ማውረድ ይችላሉ።

የኅብረት መረዳጃ ማኅበርን ስራ ለመጀመር ከሚያስፈልጉት ዋና ዋና ክንውኖች መሃል አንዱ የአባላት ምዝገባ ሂደትን ማጠናቀቅ ነው።

 ሁላችሁም እንደምታውቁት የአባልነት ማመልከቻ የምዝገባ ሂደቱ ከኤፕሪል(April 11, 2022) ፟እስከ ሜይ (May) 11 2022 ባለው ጊዜ ተካሂዶ ተጠናቋል።
ጊዚያዊ አስተዳደሩ በቂ ጊዜ ከመመደቡ ባሻገር፣ ቀኑን በማራዘም እንደዚሁም በተለያዩ ጊዜያት ተደጋጋሚ ማሳሰቢያና ማስታወሻዎች በኢሜል፣  በቴክስትና በድምጽ ስልክ ሲልክ እንደነበረ ይታወሳል። ምዝገባው በተወስነለት ጊዜ ያለመሟላት፣ ማሕበሩ በጊዜ ስራውን እንዳይጀምር

ከፍተኛ ተጽእኖ አሳድሯል። እጅግ በርካታ የሰው ሃይልም ካለአግባብ እንዲባክን አድርጓል።

ቢሆንም ግን የሕብረት መረዳጃ ማኅበር ጊዜያዊ አስተዳደር ከናንተ በቀረበለት ተደጋጋሚ የኢሜል ጥያቄ ላይ ከተወያየ በኋላ አመልካቾች አንድ የመጨራሻ እድል እንዲያገኙ በማሰብ የሚከተለውን ውሳኔ አሳልፏል።

አመልካቾች የማመልከቻ ፎርሙን (በዚህ ኢሜል ተያይዞአል) እስከ ሓምሌ 11፣ 2022 (July 11, 2022) ሞልተው እንዲልኩ።
ፎርሙን በ hmas2021@hebret.org ኢሜል ብቻ መላክ ይችላሉ።
ከአሁን እስከ ሓምሌ 11፣ 2022 (July 11, 2022) ፎርሙን የሚያስገቡ አመልካቾች፣ ከተሰጠው የጊዜ ገደብ አሳልፈው ስለላኩ፣ $75.00 ብር ቅጣት ይከፍላሉ።
የተወሰነው $75.00 ቅጣት ለወደፊት የሚከፈለው የአባልነት መመዝገቢያ ክፍያ ላይ ይጨመራል። ቅጣቱ አሁን አይሰበሰብም። በህመም ወይንም ከአገር ውጪ በመሆናቸው ቅጹን ማቅረብ ያልቻሉ አመልካቾች በቂ ማስረጃ ማቅረብ ከቻሉ ይህ ቅጣት አይመለከታቸውም።
በቅጣቱ ተስማምታችሁ ፎርሙን ከላካችሁ ኅብረት መዝገቦ ካጠናቀቅን በኋላ የኅብረትን መታወቂያ ቁጥር፤ የፖርታል መግቢያ ሊንክ፤ እንዲሁም የውክልና ቅጽ በኢሜል ይደርሳችኋል።

ይህ እስከሚሆን የአባልነት ቁጥር ያልተሞላበት የውከለና ቅጽ አንቀበልም።

ኅብረት ጊዜያዊ አስተዳደር