July 16, 2022, Robocall Message 

July 16 , 2022

አስመራጭ ኮሚቴ ለማቋቋም ከኅብረት መረዳጃ ማኅበር ጊዜያዊ አመራር የቀረበ ጥሪ

የመጀመርያ ምዝገባ ፈጽመው ነገር ግን የውክልና ቅጽ ላልላኩ አመልካቾች በሙሉ የመጨረሻ ማሳስቢያ
ኅብረት መረዳጃ ማህበር የአመልካቾችን የውክልና ቅጽ ያላሟሉትን የማረጋገጥ ሂደት እያካሄደ ይገኛል። ስለሆነም ይህ መልዕክት የደረሳችሁ አመልካቾች ሁሉ በተላከላከላቹ ፎርም የትኛውንም ቅጽ ባዶውን ሳይተዉ መረጃዎችን አሟልታችሁ ኖተራይዝድ አስደርጋችሁ በኢሜል አድራሻችን HMAS2021@HEBRET.ORG እስከ July 23, 2022 በአስቸኳይ ኢሜል እንድትልኩልን እናሳስባለን።
የውክልና ቅጽን በትክከል ተሞልቶ እስከ July 23 2022, ካልደረሰን፣ በተወሰነው ቀን ያስገቡትን የሌላውን አባላት መብት የተጋፋን ሰለመሰለን ኅብረት የአባል ጥያቄዎን ለመሰረዝ እንደምንገደድ በአጽንኦት ለማሳወቅ እንወዳለን።

ከአሁን እስከ ሓምሌ 11፣ 2022 (July 11, 2022) ፎርሙን የሚያስገቡ አመልካቾች፣ ከተሰጠው የጊዜ ገደብ አሳልፈው ስለላኩ፣ $75.00 ብር ቅጣት ይከፍላሉ።

የተወሰነው $75.00 ቅጣት ለወደፊት የሚከፈለው የአባልነት መመዝገቢያ ክፍያ ላይ ይጨመራል።
ቅጣቱ አሁን አይሰበሰብም።

በህመም ወይንም ከአገር ውጪ በመሆናቸው ቅጹን ማቅረብ ያልቻሉ አመልካቾች በቂ ማስረጃ ማቅረብ ከቻሉ ይህ ቅጣት አይመለከታቸውም።

ኅብረት ጊዜያዊ አስተዳደር

——————————————————————

ሕብረት የመረዳጃ ማኅበር ስራውን ሙሉ ለሙሉ ለመጀመር ከሚያስፈልጉት ተግባራት አንዱ የማኅበሩን አመራር (ቦርድ) ማስመረጥ ነው። ይህንን ተግባር ለማከናወን ጊዜያዊ አመራሩ በአስቸኳይ የአስመራጭ ኮሚቴ ማቋቋም ይፈልጋል።
ይህንን ኮሚቴ አቋቁሞ ስራውን እንዲጀምር ለማድረግ፣ አባላት የሚቋቋመው አስመራጭ ኮሚቴ ውስጥ በፈቃደኝነት እንዲሳተፉ ወይንም በአስመራጭ ኮሚቴው ውስጥ ለማገልገል ብቁ ናቸው የሚሏቸውን አባላት እንዲጠቁሙ በማክበር እንጠይቃለን።
አስመራጭ ኮሚቴው ውስጥ የሚያገለግሉ አባላት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
1. የኅብረትን የአባለነት ምዝገባ ያጠናቀቁ
2. በቡድን (ቲም) ውስጥ ተግባብተው መስራት የሚችሉና በኮሚቴም ሆነ በተመሳሳይ የስራ አደራጃጀት ውስጥ የመሰራት ፍላጎት ያላቸው
3. አብዛኛው የኮሚቴው ስራ የሚከናወነው በኢሜል፣ በድህረ ገጽና በተለያዩ ቴክኖሎጂ ባፈራቸው የመገናኛ ዘዴዎች በመሆኑ፣ ከዚህ ቴክኖሎጂ ጋር መለስተኛ ትውውቅ ያላቸው
4. ስራው ከአድሏዊነትና የተዛባ አሰራር የጸዳና ግልጽ በሆነ መንገድ የሚከናወን መሆን ስላለበት፣ መልካም ስነ ምግባር ያላቸውና ለሌሎችም አርአያ የሚሆኑ
ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉና በፈቃደኝነት ማገልገል የምትሹ፣ ወይንም በአስመራጭ ኮሚቴ ውስጥ ገብተው ሊያገለግሉ ይችላሉ የምትሏቸውን አባላት እስከ August 12 (ኦገስት አስራ ሁለት) ቀን ድረስ በስልክ (240) 641-4917 በመደወል ወይንም በኢሜል Elect_electioncommittee@hebret.org
በመላክ እንድትተባበሩን እንጠይቃለን። መልዕክት ስትተዉልን የምትጠቁሙትን ሰው ስምና የሰልክ ቁጥር እንድትጨምሩ እናሳስባለን።
ኅብረት መረዳጃ ማኅበር ጊዜያዊ አመራር


 

የውክልና ቅፅ ላላሟሉ አመልካቾች የተሰጠ መግለጫ –

July 12, 2022
ለኅብረት መረዳጃ ማህበር የአባልነት ምዝገባ በ07/11/2022 መጠናቀቁንና ከዚህ ቀን በኋላ መመዝገብ ማቆማችንን ማሳወቃችን ይታወሳል።
በርካታ ተመዝጋቢዎች ባቀረቡት የምዝገባ ቀን ማራዘሚያ ጥያቄ መሰረት የማኅበሩ ጊዜያዊ አመራር ተነጋግሮ የመጀምሪያውን የአባልነትጥያቄ
ማመልከቻ አቅርበው ተወካይ ማሳወቂያ ፎርም አሟልተው ላላቀረቡ ብቻ ለመጨረሻ ጊዜ የምዝገባ ቀኑን እስከ 07/30/2022 አራዝሟል።
ስለሆነም ይህ መልዕክት የደረሳችሁ አመልካቾች የውክልና ማሳወቂያ ቅጹን በተሟላ ሁኔታ ሞልታችሁ እና notarized አስደርጋችሁ
ከተጠቀሰው ቀን በፊት በኢሜል HMAS2021@HEBRET.ORG በመላክ ወይም በአካል 7961 Eastern Avenue, Suite 301
Silver Spring, MD 20910 በሚገኘው ጽ/ቤታችን በመምጣት እንድታስረክቡ እናሳስባለን።
ጽ/ቤታችን ቅዳሜ ከጠዋቱ 10 AM እስከ 4 PM ክፍት ሆኖ ይጠብቃል። በተጨማሪም የኖተሪ አገልግሎት የሚሰጡ ግለሰብ($5 በማስከፈል)
በጽ/ቤታችን ተገኝተው አገልግሎት እንዲሰጡ ማዘጋጀታችንን እንገልፃለን።
ይህ የመጨረሻ የምዝገባ ማራዘሚያ ስለሆነ ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የምታሟሉ ግለሰቦች ዕድሉን ተጠቅማችሁ ምዝገባችሁን
አንድታጠናቅቁ እናሳስባለን።
የኅብረት መረዳጃ ማህበር ጊዚአዊ አስተዳደር