June 7, 2022 – ተመዝጋቢዎች የውክልና ቅጽን በፖርታል፤በኢሜል እንዲሁም በፖስታ እንዲልኩ ብንጠይቅም የውክልና ቅጽ ማስገቢያ ጊዜውንም ብናራዝምም የብዙ ተመዝጋቢዎች የውከልና ቅጽ በምንጠብቀው መጠን እየደረሰን አይደለም። ይህ መልዕክት ከደረሰዎት እስከ ዛሬ ድረስ የውከልና ቅጽ ስላልደረሰን እንዲሁም የደረሰን የውክልና ቅጽ ያልተሟሉ ነገሮች ስላሉት ነው። ሰለሆነም፡
1) ቢሮአችን የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ (June) 11 ከጠዋቱ 4 ሰዓት (10 AM ) እስከ 10 ሰዓት
(4 PM) ይከፈታል
2) የውክልና ቅጹን በመሙላት ረገድ እንረዳለን
3) የኖታሪ አገልገሎት $5.00 ለአገልገሎት ሰጪው በመክፈል ይገለገላሉ
አመልካቾች ይህንን አገልገሎት ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉትን መረጃዎች ይዘው መምጣት አለባቸው።
1) የሁለት ተወካዮቻችሁን የመታወቂያ ቁጥር የመንጃ ፈቃድ ወይንም ፓስፖርት ቁጥር
2) የመኖሪያ አድራሻቸውን
3) የኢይሜል አደራሻን
4) የቤት ወይ የእጅ ሰልክ ቁጥር
5) የተወካዮች የሶሻል ሴኩሪቲ የመጨረሻ አራት ቁጥር ብቻ
ወደ ቢሮአችን መምጣት ለማትችሉ የውክልናውን ቅጽ ኮፒውን በፖስታ በአስቸኩዋይ (Express mail) በኅብረት አድራሻ 7961 Easter Avenue Suite # 301 Silver Spring MD 20910 መላክ፤ ወይንም ፖርታል ውስጥ በመግባት መጫን፤ ወይንም በኢሜል hmas2021@hebret.org መላክ ይችላሉ፤
አመልካቾች የውክልና ፎርሙን ለማቅረብ የተሰጣችሁ የጊዜ ገደብ እስከ ሰኔ (June) 15 ቀን ነው። የውክልና ቅጽን እስከዚህ ቀን ካልደረሰን፣ የሌላውን አባላት በተወሰነው ቀን ያስገቡትን መብት የተጋፋን ሰለመሰለን ኅብረት የአባል ጥያቄዎን ለመሰረዝ እንደሚገደዱ በአጽንኦት ለማሳወቅ ይወዳል።
ወደ ኅብረት ፖርታል እንዴት መግባት እንደሚችሉና የውክልና ቅጽን ሰለማግኘት የሚያሳየውን የቪዲዮ መመሪያ የምትቀበሉበትን የኢሜይል እና የጽሑፍ መልእክት እንዲመለከቱ እናሳሰባለን።
ማሳሰቢያ
የውክልና ቅጽን ኖተራይዝ ከተደረገ በኋላ በመሰረዝ ወይንም ደልዞ በማስተካከል ቅጽን በፖርታሉ ሰለተጫነ ወይንም ስለተላከ ህጋዊነት ሰለሌለው ቢሮ መጥተው ማስተካከል ወይንም ሌላ ንጹህ ቅጽ እንዲልኩ እናሳስባለን
አመለካቾች የውክልና ፎርሙን በትክክል ሞልተው አስገብተው ክፍያ እኪጀምሩ ድረስ ኅብረት ሥራ እንደማይጀምርና ምንም አይነት የሞት ክፍያ እንደማይፈጽም በተጨማሪም ስለ ሞት ጥያቄ መቀበልና ማስተናገድ እንደማይችል በጥብቅ እናሳውቃለን።
May 28 2022- Audio ወደ ፖርታል እንዲገቡ
May 28, 2022 :- ማህበራችን መዝገባ እስከምናጠናቅቅበት ሜይ (May) 30 ድረስ የተመዘገቡ ተመዝጋቢዎች የውክልና ቅጽን በፖርታል፤በኢሜል እንዲሁም በፖስታ እንዲልኩ ብንጠይቅም ብዙ ተመዝጋቢዎች ወደ ፖርታሉ መግባት እንዳልቻሉ ተገንዝበናል፡፡
ተመዝጋቢዎች ካጋጠሟቸው ችገሮች መሃል
1) ወደ ፖርታሉ የሚያስገባውን ሊንክ አልደረስንም ስላሉ
2) ወደ ፖርታሉ የሚያስገባው ሊንክ ደርሷቸው ፓስወርድ ለመፍጠር ሊንኩን መክፈት ስላልቻሉ
3) በአንድ ኢሜል ሁለት ሰው በመጠቀሙ ማለትም እያንዳንዱ አባል የግሉ መለያ የሆነ ኢሚል/ አስፈላጊ ስለሆነ
4) በምዝገባው ጊዜ ፎርሙን አስተካክለው ስላልሞሉ
5) የደረሰን ውክልና ቅጽ ብዙ ያልተሟሉ ነገሮች ስላሉት
6) የቀድሞ ለሁሉም ለአንድ የአባል ቁጥር ስለተጠቀሙ
7) የውክልና ቅጽን ኖተራይዝ ከተደረገ በኋላ በመሰረዝ ወይንም ደልዞ በማስተካከል ቅጽን በፖርታሉ ሰለተጫነ (ህጋዊነት ሰለሊለው)
ከላይ የተዘረዘሩትን ችግሮች ለማስወገድ ኅብረት ከዚህ በታች የሚከተሉትን ለመፈጸም ተዘጋጅቷል
1) በኅብረት ድረ ገጽ ስለ ፖርታሉ አጠቃቀም ሙሉ ስልጠና የሚሰጥ ቪዲዮ ተጭኗል፤ ሊንኩን ለማግኝት በድረ ገጽ (ሚድያ ሜኑ ላይ)፤ ወይንም ተደጋጋሚ ጥያቄና መልሶች (FAQ) https://youtu.be/m0B2lrUd7TE
2) የኅብረት ሁለት ስልክ ቁጥሮች 240-641-4917 እንዲሁም 703 455 0236 በድረ ገጽ ላይ፤ ተደጋጋሚ ጥያቄና መልሶች (FAQ), እንዲሁም ያግኙን (Contact Us) ላይ ያገኙታል
3) የውክልናውን ቅጽ ኮፒውን በፖስታ በኅብረት አድራሻ 7961 Easter Avenue Suite # 301 Silver Spring MD 20910 መላክ፤ ወይንም ፖርታል ውስጥ በመግባት መጫን፤ ወይንም በኢሜል hmas2021@hebret.org መላክ ይችላሉ፤
ከላይ በተዘረዘሩት ምክንያቶች የውክልና ወረቅት ማስገቢያውን ጊዜ ብቻ እስከ June 15 ማስረዘማችንን በትህትና እንገልጻለን.
ማሳሰቢያ
1. ኅብረት ቢሮው ቅዳሜ ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ 10 ሰዓት ከፍት ነው
የኅብረት ጊዜያዊ አስተዳደር አባላት
——————————————————————
Previous Releases – የቆዩ ማስታወቂያዎች
Jun 7, 2022- ስለ ውክልና ቅጽ አለማሟላት
May 28, 2022- መመዝገብያ ጊዜ ላሳለፉ አመልካቾች
Frequently Asked questions – ተደጋጋሚ ጥያቄዎች