የምዝገባ ክፍያ ማስታወቂያ
February 18, 2023, Robocall Message
የኅብረት መረዳጃ ማህበር ጊዜያዊ አመራር የቦርድና የመማክርት ምክርቤት አባላትን ስለመሰየሙ የተሰጠ መግለጫ
በቅድሚያ በዲሴምበር 24 2022 በተደረገ የጠቅላላ ዕጩ አመልካቾች ሰብሰባ ላይ ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት ማሕበሩን የሚመሩ የቦርድ አባላትና የመማክርት ጉባኤ አባላትን በቀጥታ የመምረጥና የመሰየም ሃላፊነት ለጊዜያዊ አመራር እንዲሰጠው መጠየቃችን የሚታወስ ነው። ሃሳቡ በተሰብሳቢ እጩ አባላት ሙሉ ድጋፍ ካገኘ በኋላ በአደረግነው እንቅስቃሴና በርካታ ዕጩ አባላት ባሳዩት ፈቃደኝነትና ትብብር እነሆ ዛሬ በቦርድና በመማክርት ምክር ቤት የሚያገለግሉ አባላትን ለመሰየም በቅተናል።
እነዚህ የቦርድ አመራር አባላት ስራቸውንም በቅርብ ለመጀመር እንዲችሉ አስፈላጊው ዝግጅት በመከናወን ላይ ይገኛል። በዚህ አጋጣሚ፣ ማህበራችንን ለማገልገልና ሰራውን በአጭር ጊዜ ለመጀመር ፈቃደኞች ለሆኑት ዕጩ ተመራጮች በሙሉ ከፍ ያለ ምስጋናችንን ማቅረብ እንፈልጋለን።
ጊዜያዊ አስተዳደሩና የሽግግር ኮሚቴው በአንድነት የዕጩዎችን የስራ ልምድ፣ የትምህርት ደረጃና በተለያዩ ሕዝባዊ ማህበራት ውስጥ ያደረጉትን አስተዋጾ ከመረመርን በኋላ ከዚህ በታች ሰማቸው የተዘረዘረው እጩ አባላት የኅብረት መረዳጃ ማኅበርን በመምራት እንዲያገለግሉ መምረጣችንን በታላቅ ደስታ እናስታውቃለን።
የቦርድ አባላት
ዶክተር ወንድም አስረስ የቦርድ ሊቀ መንበር
አቶ ፍቅሬ ሽዋቀና ተክለሃይማኖት የቦርድ ምክትል ሊቀ መንበር
ወ/ሮ ውድነሽ እውነቱ የቦርድ ፀሃፊ
አቶ አሸብር ቱፋ የቦርድ ሂሳብ ሹም
አቶ ቆርቾ ገለታ የቦርድ የህዝብ ግንኙነት
አቶ የሺዋስ አየለ የቦርድ አባል
አቶ ግርማ ለገሰ የቦርድ አባል
ዶክተር ገነነ መንግስቱ የቦርድ አባል
አቶ ዳንኤል በርሶማ ኦዲተር
የመማክርት ምክርቤት አባላት
አቶ አባተ ካሳ የምክርቤት ሊቀ መንበር
አቶ ንጋቱ ጥላሁን የምከር ቤት ምክትል ሊቀ መንበር
አቶ አንተነህ አዳሙ በቀለ የምክር ቤት ፀሃፊ
ወ/ሮ ዮክሳ ሰይፉ የምክር ቤት አባል
አቶ ዮሃንስ ኪዳኔ የምክር ቤት አባል
ወ/ሮ ጌጤነሽ ቦጋለ ተፈሪ የምክር ቤት አባል
ወ/ሮ የዝና ዘመነ ይመር የምክር ቤት አባል
ለወደፊትም ይህ አዲስ የተሰየመው ቋሚ ቦርድ የሚያከናወናቸውን ተግባራትና እንዲሁም ኅብረት መረዳጃ ማህበር ሰራውን የሚጀምርበትን ቀን በቅርቡ ለዕጩ አባላት ያስታውቃል።
የኅብረት መረዳጃ ማህበር ጊዜያዊ አመራር
December 12, 2022, Robocall Message
አስቸኳይ የኅብረት መረዳጃ ማኅበር ጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ 12/12/22
የኅብረት መረዳጃ ማኅበር ሕገ ደንብ (Bylaw) December 10 እና 11 በተደረገው የደምድ ቆጠራ 1212 እጩ አባላት ውሰጥ
898 (74%) ድምጽ ሰጥተዋል። ድምፅ ከሰጡት 898 ዕጩ አባላት 894ቱ የኅብረት መተዳደሪያ ደንቡን ሲያጸድቁ 4 ዕጩ
አባላት ተቃውሟቸውን በደምጽ አሳውቀዋል። ስለሆነም የኅብረት መተዳደሪያ ደንቡ በ99.5% ድምጽ ፀድቋል።
ከማህበራችን መተዳደሪያ ደንብ ቀጥሎ ስለሚኖሩን ተግባሮች ለመነጋገርና ውሳኔ ለመስጠት የህብረት ጊዜያዊ አስተዳደር፣ የፊታችን
እሁድ December 18, 2 PM የሚካሄደውን አጠቃላይ ጉባኤ ላይ እንዲገኙ ለማኅበሩ እጩ አባላት ሁሉ በማክበር ጥሪውን
ያቀርባል። በዚህ ስብሰባ ላይ፣ ከማኅበሩ ጊዜያዊ አመራር የእስካሁን ክንዋኔዎችን፣ ያጋጠሙ ችግሮችንና ቀጣይ የማኅበሩን የሥራ
ሂደት በተመለከተ ሪፖርት ይቀርባል :: ስለሆነም December 18, 2022 ከ 2 PM ጀምሮ በሚደረገው የዙም(zoom) ስብሰባ ላይ
በመገኘት ለማኅበሩ ሥራ መጀመር ከእርስዎ የሚጠበቀውን ወሳኝ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አጥብቀን እናሳስባለን:: በስብስባው
ለመሳተፍ የሚያስችለው አገናኝ( Link) በኢሜልና በቴክስት እንልካለን::
በስብሰባው ላይ ሁሉንም ጥያቄዎች ለመመለስ በቂ ጊዜ ላይኖረን ስለሚችል፣ ጥያቄዎቻችሁንና ሃሳቦቻችሁን ከስብሰባው በፊት
በኢሜል (hmas2021@gmail.com ) ብትልኩልን የሁላችሁንም ጥያቄና ሃሳብ በተገቢው መንገድ ማስተናገድ እንችላለን።
ይህ ጠቅላላ ጉባኤ ማኅበሩ ሥራውን በይፋ እንዲጀምር እጅግ ጠቃሚ ውይይት የምናደርግበትና ወሳኝ ውስኔ የምናሳልፍበት ቀን
ይሆናል ተብሎ ስለሚጠበቅ የአባላት መገኘትና መሳተፍ እጀግ አስፈላጊ ነው። ማኅበሩ ስራውን በቅርብ ጊዜ እንዲጀምር
የሁላችሁንም ተሳትፎ አስፈላጊነትን አጢነን ማሳሰብ እንወዳለን።
የኅብረት መረዳጃ ማኅበር ጊዜያዊ አመራር
____________________________________________
December 11, 2022, Robocall Message
12/11/2022
ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ – የኅብረት መረዳጃ ማኅበር ስራውን ለመጀመር የሚያሰችለውን የመተዳደሪያ ደንብ ለማጽደቅ የወጣ ጥብቅ ማሳሰቢያ።
እጩ አባላት ኅብረት መረዳጃ ማህበር ስራውን ለመጀመር እንዲችል መጠናቀቅ ካላባቸው አበይትና ወሳኝ ተግባራት አንዱ የመተዳደሪያ ደንቡን ማጽደቅ እንደሆነ አጥብቀን ለማስታወስ እንወዳለን። ሰለሆነም በተሰጠው የጊዜ ገደብ ትናንት December 10, 2022, ከጠዋቱ 9AM የጀመረው ድምጽ የመስጠት ኂደት ዛሬ December 11, 2022 5PM ላይ እንደሚጠናቀቅ እየገለጽን ድምጽዎን እንዲሰጡ በትህትና እናሳስባለን። በምርጫው ቀን ከ evote@securedvoting.awsapps.
ማሳሰቢያ
እጩ አባላት ማህበሩ ስራውን መቼ እንደሚጀምር ለመጠየቅ በተደጋጋሚ መልዕክት ይደርሰናል ይህንን በተመለከተ የጠቅላላ ጉባኤ ሰብሰባ በቅርቡ እንደምንጠራ እናሳውቃለን።
የኅብረት ጊዜያዊ አመራር
_____________________________________
12/10/2011
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የኅብረት መረዳጃ ማኅበር ስራውን ለመጀመር የሚያሰችለውን የመተዳደሪያ ደንብ ለማጽደቅ የወጣ ጥብቅ ማሳሰቢያ። ማሳሰቢያ _______________________________________
12/01/2022 የኅብረት መረዳጃ ማኅበር ስራውን ለመጀመር የሚያሰችለውን የመተዳደሪያ ደንብ |
Previous Releases – የቆዩ ማስታወቂያዎች
December 24, 2022-General Assembly
December 23, 2022-General Assembly
December 18, 2022-General Assembly
December 12, 2022-Vote the Bylaw
December 11, 2022-Vote the Bylaw
December 10, 2022-Vote the Bylaw
December 01, 2022-Vote the Bylaw
october 9, 2022- Election Comittee
September 10፣ , 2022- ክፍያ አንቀበልም
Sep 4, 2022- የአንድ ጊዜ መዋጮ መሰብሰብ
July 22, 2022- የአስመራጭ ኮሚቴ ማቋቋም
July 2 2022- ሳይመዘገቡ የውክልና ቅጹን ለላኩ
July 1, 2022- ስለ ውክልና ቅጽ አለማሟላት
July 12, 2022- ምዝገባ የማናደርግ መሆናችንን
Jun 26, 2022- መመዝገቢያ ጊዜ ላሳለፉ አመልካቾች
Frquently Asked questions – ተደጋጋሚ ጥያቄዎች